ቀጥታ፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ አዲስ ዓመትን በማስመልከት ማዕድ አጋሩ 

አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦ከንቲባ አዳነች አቤቤ አዲስ ዓመትን በማስመልከት በልደታ ተስፋ ብርሃን ምገባ ማዕከል ማዕድ አጋርተዋል።


 

በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት በማዕከሉ ምገባ ዘወትር የሚከናወን ቢሆንም፣ በዛሬው ዕለት በበዓሉ ምክንያት የተገኘነው ለእናንተ ያለንን አክብሮት፣ ፍቅርና ቤተሰባዊነት ለመግለፅ ነው ብለዋል። 


 

አዲሱ ዓመት የበለጠ የምንደጋገፍበትና የምንበለፅግበት እንዲሆን እመኛለሁ በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም