የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ለአዲሱ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ - ኢዜአ አማርኛ
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ለአዲሱ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ለ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ሊቀመንበሩ በመልዕክታቸው፣ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት እንኳን አደረሳችሁ በማለት ልባዊ ምኞታቸውን ገልጸዋል።
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ከኢትዮጵያ ህዝብ በአብሮነት መቆሙን እንደሚቀጥል የገለጹ ሲሆን ሀገሪቷ ለአፍሪካ አንድነት፣ ነፃነትና የጋራ ውጥኖች ስኬት ያላትን ታሪካዊ አበርክቶ አድንቀዋል።
አዲሱ ዓመት ለኢትዮጵያ ህዝብ የሰላም፣ የፍቅርና የብልጽግና እንዲሆን ተመኝተዋል።
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን አንድነቷ የተጠበቀ፣ ሰላማዊና የበለጸገች አፍሪካን ለመገንባት በቁርጠኝነት መስራቱን እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።