ኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመትን እያከበሩ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመትን እያከበሩ ነው
አዲስ አበባ፤ መስከረም 1/2019 (ኢዜአ) :- ኢትዮጵያውያን የ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመትን ተቀብለው በማክበር ላይ ይገኛሉ።
የኢትዮጵያውያን የዘመን መለወጫ የሆነው መስከረም አንድ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል።
የሃይማኖት አባቶች ባስተላለፉት መልዕክት፣ ኢትዮጵያውያን የ2019 ዘመን መለወጫ በዓልን አብሮነትን በማጠናከርና የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት ሊያከብሩት እንደሚገባ ገልጸዋል።
በሀገር ውስጥ እና በውጭ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን በሙሉ ለአዲሱ አመት የዘመን መለወጫ በዓል እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል።
የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችም አዲሱ ዓመት የሰላም፣የፍቅር፣ የብልጽግናና ደስታ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
መንግስት በ2018 ዓ.ም የተመዘገቡ ስኬቶችን በአዲሱ ዓመት አጠናክሮ ለማስቀጠል እንደሚሰራም አስታውቋል።