ቀጥታ፡

ፊነርባቼ ከሮማ፣ ፒኤስቪ ከሻካታር ዶኔስክ ያደረጓቸው ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀቁ

አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሊግ ምዕራፍ ጨዋታዎች መካሄዳቸውን ቀጥለዋል።

ማምሻውን በሱክሩ ሳራኮግሉ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፊነርባቼ እና ሮማ ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።

አርቺ ብራውን ለፊነርባቼ፣ ብራያን ክሪስታንቴ ለሮማ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

በፊሊፕስ ስታዲየም በተደረገው ሌላኛው መርሐ ግብር ፒኤስቪ አይንድሆቨን ከሻካታር ዶኔስክ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

ሰርጂኖ ዴስት ለፒኤስቪ ግቧን ሲያስቆጥር ግሊከር ሜንዶዛ የሻካታርን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም