ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ ከ600 በላይ እስረኞች በይቅርታና ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር ተለቀቁ - ኢዜአ አማርኛ
ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ ከ600 በላይ እስረኞች በይቅርታና ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር ተለቀቁ
አዲስ አበባ፤ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በሀይል ለመናድ ሞክረዋል በሚል ታስረው የነበሩ ግለሰቦች እንዲፈቱ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ከመንግስት ጋር ላለፉት 5 ወራት ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን አስታውቋል።
በፍርድ ቤት ውሳኔ ታሰረው የነበሩት በይቅርታ፣በክስ ሂደት ላይ የነበሩት ደግሞ ክሱ እንዲቋረጥ ተደርጎ ከ6 መቶ በላይ እስረኞች በዛሬው እለት እንዲፈቱ መደረጉን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ ለኢቢሲ ገልጸዋል።
ይህ ቁጥር ክልሎች በየራሳቸው ከሚፈቷቸው ውጭ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ የተፈቱት እስረኞች ከአማራና ከኦሮሚያ በፌደራል ደረጃ የታሰሩ እንደነበሩም ተነግሯል።
በይቅርታ ከመፍታትና ክስ ከማቋረጥ በተጨማሪም በህግ የታገዱ መብቶቻቸው እንዲመለሱ መደረጉ ተገልጿል።
በተመሳሳይ መዝገብ የሚገኙ 28 የሚሆኑ እስረኞች የይቅርታ ጥያቄ ባለማቅረባቸው ከእስር አለመፈታታቸውን ኢሰመኮ አስታውቋል።