ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለአዲሱ ዓመት ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡-

👉 ዘመን በፈጣሪ የተሰጠ የመሥሪያ መጽሐፍ በመሆኑ፤ ትናንት የጻፍናቸውን የውድቀትና የድል ታሪኮች በማስታወስ ዛሬ ላይ ሆነን የተሻለ ጽሑፍ መጻፍ ይገባል።

👉 በግብርና (በበጋ ስንዴና ሌማት)፣ በኢኮኖሚ፣ በአረንጓዴ ልማት እና በግዙፍ ፕሮጀክቶች እየታዩ ያሉ ስኬቶች የኢትዮጵያን የነገ ብልጽግና እያረጋገጡ ናቸው።

👉 የጠላት ሟርት ከሽፎ ሕዝቡ በባለቤትነት በተሳተፈበት ሀገራዊ ምክክር ሰፊ መግባባት ላይ መደረሱ እና ለዚህም ማሳያ የሚሆን የታራሚዎች የምሕረት ይቅርታ ተደርጓል።

👉 የጉልበትና የጠመንጃ ጊዜ አብቅቶ የብዕር፣ የሐሳብና የሰላም ጊዜ በመተካቱ ቀጣዩ የኢትዮጵያ ምዕራፍ በንግግርና በመግባባት ላይ የተመሠረተ ይሆናል።

👉 ሀገራዊ ምክክሩ ልሂቃን ብቻ የሚደራደሩበት ሳይሆን ገበሬው፣ አርብቶ አደሩ፣ ወጣቱና ሴቱ በቀጥታ ተሳትፈው የሀገራቸውን ዕጣ ፈንታ በባለቤትነት የወሰኑበት ታሪካዊ ምዕራፍ ሆኗል።

👉 የኢነርጂ አቅምን ከማሳደግ ባለፈ ዲጂታል 2030ን ስኬታማ በማድረግ ረገድ የተጀመሩ ሥራዎች የሀገሪቱን የቴክኖሎጂና የኢኮኖሚ አድማስ እያሰፋ ነው።

👉 የቢሾፍቱ ግዙፍ አየር ማረፊያ ፕሮጀክት እና የኮሪደር ልማቶች የኢትዮጵያን ሀብት፣ ገጽታና ውበት ለዓለም እያስተዋወቁ ናቸው።

👉 የኢትዮጵያ የብልጽግና እና የሰላም ጉዞ ስኬት የተሳካ እንዲሆን የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የጸጥታ ተቋማት፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ሚዲያዎች እና የሲቪል ሰርቫንቱ የተቀናጀ ተሳትፎ ወሳኝ ነው።

👉 የኢትዮጵያ የባሕር በር አጀንዳ ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነትን አግኝቶ የሀገሪቱን የተጽዕኖ አድማስ እያሰፋው መጥቷል።

👉 አዲሱ ዓመት የፖለቲካ ምኅዳሩ ሰፍቶ፣ ኅብረ ብሔራዊ አንድነቱ የጸና እና ምርታማነቱ በዓይነትና በጥራት የጨመረበት የብልጽግና ትውልድ መገንቢያ ዘመን እንዲሆን ታቅዷል።

👉 በምክክሩ የተግባባንባቸው ሐሳቦች ባህል፣ ሥርዓት፣ አሠራር፣ ዐዋጅ እና ሕገ መንግሥታዊ ማሻሻያ ሆነው መሬት ላይ ወርደዋል።

👉 በአዲስ ዓመት ዋዜማ በምሕረት የተፈቱ ታራሚዎች ካለፈው ተምረው በሀገር ሰላምና ልማት ላይ አዎንታዊ አስተዋጽኦ ያደርጉ ዘንድ ማኅበረሰቡ ሊደግፋቸው ይገባል።

👉 የተደረጉ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች የዘመናትን የኢኮኖሚ ስብራት በመጠገን የምርትና የወጪ ንግድ ጭማሪን እያመጡ ነው።

👉 በ"ኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ ማኑፋክቸሪንግን እየገነባ ሲሆን፣ የሀገር ውስጥ የመድኃኒት ማምረት አቅምም እያደገ መጥቷል።

👉 የወንዝ ዳርቻ ልማቶች አፈርን፣ ከተማዎችን፣ የውኃ ሀብትን እና ጤናን በአንድ ላይ እየጠበቁ ነው።

👉 የማዕድን ፍለጋ፣ ምርትና ሽያጭ እንቅስቃሴዎች ከቀድሞው የተሻለ አፈጻጸም እያሳዩ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም