የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የመደጋገፍ እሴትን እያጎለበተ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የመደጋገፍ እሴትን እያጎለበተ ነው
ሆሳዕና ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የመደጋገፍ እሴትን እያጎለበተ መሆኑን የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ።
የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሃላፊ ጌታቸው ሌሊሾ፤ በክልሉ የክረምት የበጎ ፈቃድ በርካታ ወጣቶች የተለያዩ አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በክልሉ ዘንድሮ በ15 ዘርፎች ከ2 ሚሊየን 700 ሺህ በላይ በጎ ፈቃደኞች የተሳተፉበት የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እየተተገበረ ይገኛልም ብለዋል።
በክረምቱ የ2 ሺህ 7 አቅመ ደካሞችን ቤቶችን ለመገንባት ታቅዶ እስካሁን ከ1 ሺህ 800 በላይ ገንብቶ ማስረከብ መቻሉን ተናግረዋል።
በዛሬው እለትም የክልሉ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ በሀድያ ዞን ፎንቆ ከተማ ያስገነባቸውን ቤቶች ለነዋሪዎች ማስረከቡን ገልጸዋል።
የእድሉ ተጠቃሚ የሆኑ ነዋሪዎች ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።