የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ - ኢዜአ አማርኛ
የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ
ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ገለጹ።
ጳጉሜን 5 የነገው ቀን በአማራ ክልል በተለያዩ መርሃ ግብሮች እየተከበረ ይገኛል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የክልሉ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፤ የነገውን የሀገርን ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ብለዋል።
የዛሬው ትጋታችን ለነገ ከተስፋም ባለፈ ፍሬ የሚያፈራ በመሆኑ በሁሉም ረገድ የጀመርናቸው የልማት ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አፅኖት ሰጥተዋል።
የክልሉ መንግሥት የነገውን ትውልድና የሀገር ተስፋ በማሰብ የአሻጋሪ ዕድገት እና የዘላቂ ልማት አቅዶችን ለማሳከት የተቀናጀ ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
የነገ ዋስትናችን ዛሬ በመሆኑ የቀጣዩን ትውልድ ተስፋ ለማሳመር በቴክኖሎጂና ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች ላይ በማተኮር መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።
ርእሰ መስተዳድሩ በማጠቃለያ መልእክታቸው አዲሱ ዓመት ለክልሉ ህዝብና ለመላው ኢትዮጵያዊያን የሰላም፣ የፍቅርና የስኬት እንዲሆን ተመኝተዋል።