ቀጥታ፡

በክልሉ የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረግ ጥረት ይቀጥላል

አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረግ ጥረት ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን በብልጽግና ፓርቲ የክልሉ ቅርንጫፍ ጽህፈት ኃላፊ ኢሳቅ አብዱልቃድር ተናገሩ።

የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጳጉሜን 5 (የነገ ቀን) ምክንያት በማድረግ በአሶሳ ከተማ የግራናይት ፋብሪካ እና የቀርከሃ ፋብሪካዎች የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል።


 

በጉብኝቱ ላይ የተገኙት በብልጽግና ፓርቲ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኢሳቅ አብዱልቃድር፤ በክልሉ የተጀመሩ ሁለንተናዊ የልማት ስራዎች ትልቅ ተስፋ የተሰነቀባቸው መሆኑን ገልጸዋል።

በጉብኝቱ ያረጋግጥነው ይህንኑ ነው ያሉት ሃላፊው በክልሉ የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረግ ጥረት ይቀጥላል ብለዋል።

በክልሉ በተለይም ወጣቶች የስራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑና በዲጂታል ቴክኖሎጂ የዳበረ እውቀት እንዲኖራቸው ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን አንስተዋል።

ባለፋት ዓመታት የተከናወኑ የልማት ስራዎች የነገዋን ኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ የሚያረጋግጡ መሆናቸውን እና የዜጎችን ተጠቃሚነት በተግባር ያሳዩ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

በክልሉ የግብርናውን፣ ማዕድንና የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት እየተመዘገበ እንደሆነም ተናግረዋል።


 

በመርሃ ግብሩ በክልሉ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ጉዞ እና የኢንቨስትመንት አማራጮችን ማልማት ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት ተካሂዷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም