ቀጥታ፡

ባየር ሙኒክ ከቦዶ ግሊምት እና ማንችስተር ዩናይትድ ከሳባህ: የዕለቱ ተጠባቂ መርሐ ግብሮች

አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ):- የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሊግ ምዕራፍ የመጀመሪያ ዙር መርሐ ግብር ዛሬ ይጠናቀቃል።

ባየር ሙኒክ የኖርዌውን ቦዲ ግሊምት ምሽት አራት ሰዓት ላይ በአሊያንዝ አሬና ስታዲየም ያስተናግዳል።

የስድስት ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ባለቤቱ ባየርን ባለፈው የውድድር ዓመት እስከ ግማሽ ፍጻሜ ደርሷል።

በሻምፒዮንስ ሊጉ የሊግ ምዕራፍ ለሁለተኛ ጊዜ የሚሳተፈው ቦዶ ግሊምት ባለፈው የውድድር ዓመት 16 ውስጥ ገብቷል።

ቦዶ ግሊምት በጉዞው ማንችስተር ሲቲ፣ አትሌቲኮ ማድሪድ እና ኢንተር ሚላን ያሸነፈበት መንገድ በእግር ኳስ አፍቃሪያን አድናቆት አስችሮታል።

በዛሬውም ጨዋታም ሙኒክን ይፈትነዋል ተብሎ ይጠበቃል።




በሌላኛው መርሐ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ ከሳባህ ምሽት አራት ሰዓት ላይ በኦልድትራፎርድ ስታዲየም ይጫወታሉ።

የሶስት ጊዜ የሻምፒዮንስ ሊግ ሻምፒዮኑ ማነችስተር ዩናይትድ ከእ.አ.አ 2023/24 የውድድር ዓመት በኋላ ወደ አውሮፓ መድረክ ተመልሷል።

እ.አ.አ በ2017 የተመሰረተው የአዘርባጃኑ ሳባህ ለመጀመሪያ ጊዜ በሻምፒዮንስ ሊጉ ተሳትፎ ያደርጋል።

በሌሎች መርሐ ግብሮች በሻምፒዮንስ ሊጉ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሳተፈው የጣልያኑ ኮሞ ከአርቢ ላይፕዚግ እና ስላቪያ ፕራግ ከሌንስ በተመሳሳይ ምሽት አራት ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ፊነርባቼ ከሮማ እና ፒኤስቪ አይንድሆቨን ከሻካታር ዶኔስክ በተመሳሳይ ምሽት 1 ሰዓት ከ45 ላይ ይጫወታሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም