ቼልሲ በካራባኦ ካፕ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈ - ኢዜአ አማርኛ
ቼልሲ በካራባኦ ካፕ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈ
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ)፦ የእንግሊዝ ካራባኦ ካፕ ሶስተኛ ዙር መርሐ ግብር ቼልሲ ከመመራት ተነስቶ ሊድስ ዩናይትድን 6 ለ 3 አሸንፏል።
ማምሻውን በስታምፎርድ ብሪጅ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኮል ፓልመር (አንዱ በፍጹም ቅጣት ምት) እና ዳኒ ዌልቤክ በተመሳሳይ ሁለት ግቦችን አስቆጥረዋል።
ፔድሮ ኔቶ እና ቫለንቲን ባርኮ ቀሪዎቹን ግቦች ለሰማያዊዎቹ ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ታሪክ ሙሃሬሞቪች፣ ብሬንደን አሮንሰን እና ዶምኒክ ካልቨርት-ሉዊን ለሊድስ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ሊድስ ዩናይትድ በመጀመሪያ አጋማሽ አጋማሽ 2 ለ 0 በመምራት ከሜዳ ቢወጣም ቼልሲ ከእረፍት መልስ ስድስት ግቦችን በማስቆጠር ውጤቱን ቀልብሷል።
ዘጠኝ ጎሎች በተቆጠሩበት ጨዋታ ቼልሲ በሊጉ በአርሰናል ካጋጠመው ሽንፈት በኋላ ወደ ድል መንገድ ተመልሷል።
ውጤቱን ተከትሎም ቼልሲ ወደ አራተኛ ዙር አልፏል።
ሊድስ ዩናይትድ የካራባኦ ካፕ ጉዞው ሶስተኛ ዙር ላይ ተገቷል።