ቀጥታ፡

የ2019 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በሰባት ስታዲየሞች ይደረጋል

አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 4 /2018 (ኢዜአ)፦ የ2019 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በተመረጡ ሰባት ስታዲየሞች እንደሚካሄድ የሊጉ አክሲዮን ማህበር አስታወቀ።

የሊጉ ጨዋታዎች የእጣ ማውጣት ስነ ስርዓት መስከረም 7 ቀን 2019 ዓ.ም ይከናወናል።

መስከረም 30 የሚጀምረው የ2019 ዓ.ም የሊጉ ውድድር በተመረጡ ሰባት ሜዳዎች እና በተዘጋጁ ስድስት ቋቶች በሚወጣው እጣ መሰረት የውድድር ዓመቱ መርሃ ግብር ይዘጋጃል።

አዲስ አበባ ስታዲየም፣ አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም፣ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ባህርዳር አለም አቀፍ ስታዲየም፣ሀላባ ስታዲየም፣ ሆሳዕና አብዩ ኤርሳሞ ስታዲየም እና አርባምንጭ ዩንቨርሲቲ አባያ ካምፓስ ስታዲየም ውድድሩ የሚካሄድባቸው ሜዳዎች ናቸው።

በውድድሩ ላይ 18 ክለቦች እንደሚሳተፉ የሊጉ አክሲዮን ማህበር መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም