የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የሚጀመርበት ጊዜ ላይ ማሻሻያ ተደረገ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የሚጀመርበት ጊዜ ላይ ማሻሻያ ተደረገ
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ):- የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ2019 ዓ.ም የውድድር ዘመን ጥቅምት 8 ቀን 2019 ዓ.ም እንደሚጀመር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።
ፕሪሚየር ሊጉ መስከረም 7 ቀን 2019 ዓ.ም እንደሚጀመር ተገልጾ ነበር።
ይሁንና አብዛኞቹ ክለቦች ዝግጅት ባለመጀመራቸው እና በሴቶች ብሔራዊ ቡድኑ የኦሊምፒክ ማጣሪያ ዝግጅት ምክንያት ሊጉ የሚጀመርበት ቀን ጥቅምት 8 2019 ዓ.ም እንዲሆን መወሰኑን ፌዴሬሽኑ አመልክቷል።