ቀጥታ፡

በክልሉ የአብሮነት እሴቶችን በማጠናከር ለዘላቂ ሰላምና ልማት ለማዋል ትኩረት ተሰጥቷል   

ሳጃ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በክልሉ የአብሮነት እሴቶችን በማጠናከር ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ ትኩረት መሰጠቱን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቡቶ አኒቶ ገለፁ።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጳጉሜን - 4 የሕብር ቀን "ብዝኃነት የኢትዮጵያ ጌጥ" በሚል መሪ ቃል በክልል ደረጃ በሳጃ ከተማ በማስ ስፖርት፣ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖችን ማዕድ በማጋራት እና በፓናል ወይይት ተከብሯል ።


 

በዚህ ወቅት የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ አቡቶ አኒቶ እንደተናገሩት፣ በክልሉ  የአብሮነት እሴቶችን በማጠናከር ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው፡፡

የሕብር ቀን መከበሩም እርስ በርስ የመረዳዳትና የመተሳሰብ እሴቶችን በማሳደግ ማህበራዊ ትስስርን ለማጠናክር ማገዙን ገልጸዋል፡፡

በክልሉ ያሉ የብዝሀነትና የአብሮነት እሴቶችን በማጉላት ለዘላቂ ሰላምና ልማት መጠናከር ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑንም አስረድተዋል።

የየም ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሽመልስ እጅጉ በበኩላቸው ፤ሕብረ ብሔራዊ አንድነትን ለማጎልበት የጋራ እሴቶች ማጠናከር እና የወል ትርክት  ግንባታ ላይ ማተኮር ይገባል ብለዋል። 


 

ሕብረ ብሔራዊ አንድነትን ማጠናከር ሠላምን በዘላቂነት ለማስፈንና ልማትን ለማስቀጠል ከፍተኛ አቅም መፍጠሩን ተናግረዋል።

ይህም  ፈተናዎችን  ወደ ድል  በመቀየር  የኢትዮጵያን  ማንሰራራት  ለማፋጠን  አዎንታዊ ሚና እየተጫወተ መሆኑን  ገልጸዋል፡፡

የአብሮነት እሴቶችን በማጉላት የተገኙ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ስኬቶችን ማስቀጠል ይገባል ያሉት ደግሞ የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል መንገሻ ናቸው።


 

ለዚህም  የህዝቦችን የአብሮነትና የመከባበር እሴቶች ይበልጥ አጎልብቶ ጥቅም ላይ በማዋል የኢትዮጵያን ከፍታ ማላቅ ይገባል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም