ቀጥታ፡

ፒኢስጂ ከስሎቫን ብራቲስላቫ፣ ናፖሊ ከአርሰናል እና ሊቨርፑል ከአትሌቲኮ ማድሪድ፤ የዕለቱ ተጠባቂ ጨዋታዎች

አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ):- በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዛሬ ስድስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

ምሽት አራት ሰዓት ፒኤስጂ ከስሎቫን ብራቲስላቫ በፓርክ ደ ፕሪንስ ይጫወታሉ።

የፈረንሳዩ ፒኤስጂ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግን ለተከታታይ ጊዜ ያነሳ ክለብ ነው።




የስሎቫኪያው ስሎቫን ብራቲስላቫ በአዲሱ የውድድር ፎርማት ለሁለተኛ ጊዜ ይሳተፋል።

የአውሮፓ ታላቁን ክብር ለሶስተኛ ጊዜ ለማንሳት ያለመው ፒኤስጂ ክብሩን የማስጠበቅ ጉዞውን ዛሬ ይጀምራል።

በሌላኛው መርሐ ግብር ናፖሊ ከአርሰናል በዲያጎ አርማንዶ ማራዶና ስታዲየም ምሽት አራት ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።




የባለፈው ዓመት የሻምፒዮንስ ሊግ የፍጻሜ ተፋላሚ የሆነው አርሰናል ከጣልያኑ ክለብ በሚያደርገው ጨዋታ የሊግ ምዕራፍ ውድድሩን ይጀምራል።

ናፖሊ ባለፈው የውድድር ዓመት በሊግ ምዕራፉ ላይ የተሰናበተ ሲሆን ዘንድሮ በጥሩ ሁኔታ ለመጀመር የለንደኑን ክለብ ያስተናግዳል።

ምሽት አራት ሰዓት ላይ ሊቨርፑል ከአትሌቲኮ ማድሪድን በአንፊልድ ሮድ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያከናውናሉ።

ሊቨርፑል የስድስት ጊዜ የውድድሩ አሸናፊ ነው። አትሌቲኮ ማድሪድ ሁለት ጊዜ ለፍጻሜ ደርሶ ተሸንፏል።

ጨዋታው ጠንካራ ፉክክር ይታይበታል ተብሎ ይጠበቃል።

ባርሴሎና ከፌይኖርድ ሮተርዳም እና ስቱትጋርት ከቫይኪንግ ኤፍሲ በተመሳሳይ ከምሽቱ 1 ሰዓት ከ45 ላይ ይጫወታሉ።

ምሽት አራት ሰዓት ላይ ስፖርቲንግ ሊዝበን ከጋላታሳራይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም