ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የ2018 ኮከቦች ሽልማት ተካሄደ

አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 3/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የ2018 ዓ.ም የውድድር ዘመን የሽልማት እና እውቅና መርሐ ግብር ዛሬ ማምሻውን ተከናውኗል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንኳ እመቤት አዲሱ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ተጫዋች በመሆን የ120 ሺህ ብር ተሸልማለች።

በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ግብ አግቢ 24 ግቦችን ያስቆጠረችው የኢትዮ ኤሌክትሪኳ ዳግማዊት ሰለሞን  ኮከብ ግብ አግቢ በመሆን የ120 ሺህ ብር ተሸላሚ ሆናለች።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንኳ ታሪኳ በርገና የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ግብ ጠባቂ በመሆን የ120 ሺህ ብር ሽልማት አግኝታለች።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንኩ አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ አሰልጣኝ በመሆን ተመርጧል።

ፌደራል ዋና ዳኛ ቤተልሔም ማሞ የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ምስጉን ዋና ዳኛ በመሆን የ100 ሺህ ብር ተሸላሚ ሆናለች።

የሀላባ ከተማው ያሬድ መሀመድ የከፍተኛ ሊግ የውድድር ዓመቱ ኮከብ ተጫዋች በመሆን የ100 ሺህ ብር ተሸላሚ ሆኗል።

የደሴ ከተማው አማኑኤል ግዛቸው 10 ግቦችን በማስቆጠር የከፍተኛ ሊግ ኮከብ ግብ አግቢ በመሆን 100 ሺህ ብር ተሸልሟል።

የጋሞ ጨንቻው መኮንን መርዶኪዮስ የከፍተኛ ሊግ ኮከብ ግብ ጠባቂ በመሆን የ100 ሺህ ብር ተሸላሚ ሆኗል።

የጋሞ ጨንቻው አሰልጣኝ ማቴዎስ ለማ የከፍተኛ ሊግ ኮከብ አሰልጣኝ በመሆን የ100 ሺህ ብር ተሸልሟል።

መሐመድ አብዱልአዚዝ የኢትዮጵያ ሊግ አንድ የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች በመሆን ተመርጦ የ75 ሺህ ብር ሽልማት አግኝቷል።

የሲዳማ ቡና ተጫዋች ናትናኤል ካሳሁን የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪሚየር ሊግ የወድድሩ ኮከብ ተጫዋች በመሆን የ70 ሺህ ብር ተሸላሚ መሆን ችሏል።

የቀድሞ ኢንተርናሽናል ዳኛ የነበሩት ኃይለመላክ ተሰማ ለስፖርቱ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የልዩ ሕይወት ዘመን ተሸላሚ በመሆን ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በሌላ በኩል ኢንስትራክተር ሽፈራው እሸቱ ለዘመናት ላበረከቱት ላቅ ያለ አስተዋጽኦ ሌላኛው የልዩ ሕይወት ዘመን ተሸላሚ በመሆን ተሸልመዋል።

በተጨማሪም በተለያዩ ዘርፎች ሽልማት ተበርክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም