የባሎን ዶር ሽልማት እጩዎች ይፋ ሆኑ - ኢዜአ አማርኛ
የባሎን ዶር ሽልማት እጩዎች ይፋ ሆኑ
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 3/2018 (ኢዜአ):- የፍራንስ ፉትቦል መጽሔት ከአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር (ዩኤፋ) ጋር በመተባበር የዘንድሮው የባሎን ዶር ሽልማት እጩዎች ዛሬ ይፋ አድርገዋል።
በዚሁ መሰረት በወንዶች ሲጠበቅ የነበረው የ30 ተጫዋቾች ዝርዝር ይፋ ሆኗል።
ጁድ ቤሊንግሃም፣ ፓው ኩባርሲ፣ ማርክ ኩኩሬያ፣ ኡስማን ደምቤሌ ፣ ሉዊዝ ዲያዝ፣ ብሩኖ ፈርናንዴስ እና ጋብሪኤል ማጋሌስ ተካተዋል።
አርሊንግ ሃላንድ፣ አሽራፍ ሃኪሚ፣ ሃሪ ኬን፣ ክቪቻ ክቫራትስኬሊያ፣ ሳዲዮ ማኔ፣ ማርኪኒዮስ፣ ላውታሮ ማርቲኔዝ እና ኪሊያን እምባፔ እጩ ተጫዋቾች ናቸው።
ኑኖ ሜንዴዝ፣ ሊዮኔል ሜሲ፣ ጆአዎ ኔቬስ፣ ማይክል ኦሊሴ፣ ዊሊያም ፓቾ፣ ጁሊያን ኪንዮኔዝ፣ ዴክላን ራይስ እና ሮድሪ እጩ ሆነዋል።
ፋቢያን ሩዊዝ፣ ዊሊያም ሳሊባ፣ ፌራን ፓሬስ፣ ዳዮ አፕሜካኖ፣ ቪኒሺየስ ጁኒየር፣ ቪቲንሃ እና ላሚን ያማል ዝርዝር ውስጥ ተካተዋል።
ኡስማን ደምቤሌ የወቅቱ የባሎን ዶር አሸናፊ ነው።
ከወንዶች በተጨማሪ የሴቶች 30 ዕጩ ተጫዋቾችም ይፋ ሆነዋል።
እንደ ሴልማ ባቻ፣ ባርባ ባንዳ፣ ማሮና ካልደንቴይ፣ መርቺ ዱሞርናይ ፣ ካሮሊን ግራም ሀንሰን፣ አሌክሲያ ፑቴላስ እና ማፓ ሌን የመሳሰሉ ከዋክብት በዝርዝሩ ውስጥ ይገኛሉ።
በምርጥ አሰልጣኞች (ዮሐን ክራይፍ ትሮፊ) በወንዶች ሚኬል አርቴታ፣ ሉዊስ ዴ ላ ፉንቴ ፣ ኡናይ ኤምሬ፣ ቪንሰንት ኮምፓኒ እና ሉዊስ ኤንሪኬ ( ፒኤስጂ) በእጩነት ቀርበዋል።
በወንዶች ምርጥ ጠባቂ (ያሲን ትሮፊ) ቮዚኒሀ፣ ያሲን ቦኖ፣ ዴቪድ ራያ፣ ማትቬይ ሳፎኖቭ ፣ቲቦ ኮርቶዋ፣ ሁዋን ጋርሺያ፣ ግሬጎር ኮቤል፣ ኤሚሊያኖ ማርቲኔዝ፣ ኤድዋርድ ሜንዲ እና ኡናይ ሲሞን እጩ ሆነዋል።
ያን ዲዮማንዴ፣ ላሚን ያማል፣ ከሪም አላሄጎቪች ፣ አዩብ ቡአዲ፣ፓው ኩባርሲ፣ኢብራሂም ማዛ፣ ዮሃን ማንዛምቢ፣ ጁኒየር ክሩፒ፣ ዋረን ዛየር ኤምሬ እና ሌናርት ካርል የዓመቱ ምርጥ ወጣት ተጫዋች (ኮፓ አዋርድ) የተካተቱ ተጫዋቾች ናቸው።
አርሰናል፣ ባየር ሙኒክ፣ባርሴሎና፣ ፍላሚንጎ እና ፒኤስጂ ለምርጥ ክለብነት ሽልማት እጩ በመሆን ቀርበዋል።
እጩዎቹ የተመረጡት ከእ.አ.አ ኦገስት 3 2025 እስከ ጁላይ 19 2026 ያሳዩትን ብቃት መሰረት በማድረግ ነው።
የተጫዋቾች መምረጫ መስፈርት የሚዘጋጀው በፍራንስ ፉትቦል መጽሔት እና ለኪፕ ጋዜጣ ነው።
የ30ዎቹ እጩዎች ዝርዝር የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር (ዩኤፋ) ታዋቂ አምባሳደሮች እንዲሁም ባለፈው ዓመት በድምፅ አሰጣጥ ትክክለኝነት ከፍተኛ ውጤት ባስመዘገቡ ዓለም አቀፍ የስፖርት ጋዜጠኞች የጋራ ጥልቅ ምክክር ይፋ የሚሆን ነው።
የባሎን ዶር እጩ መሆኛ መስፈርቶች የተጫዋች የግል ብቃት ወጥነት እና ያስቆጠሯቸው ግቦች፣ ከክለብ እና ከብሔራዊ ቡድን ጋር ባገኟቸው የዋንጫ ስኬቶች፣ እንዲሁም በሜዳ ውስጥና ከሜዳ ውጭ የሚያሳዩት ስነ ምግባር እና ለስፖርት መርሆዎች ተገዢነት ናቸው።
የባሎን ዶር ሽልማት ዘንድሮ ለ70ኛ በእንግሊዝ ለንደን ከተማ ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ.ም ይካሄዳል።
የእግር ኳስ ዓለም ከፍተኛ ክብር የሆነው እና በፍራንስ ፎትቦል መጽሔት አማካኝነት እ.አ.አ በ1956 ያደረገው የባሎን ዶር ሽልማት በወንዶችና በሴቶች እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ታላላቅ የሜዳ ላይ ገድሎችን ሲዘክር ቆይቷል።