የካራባኦ ካፕ የሶስተኛ ዙር መርሐ ግብር ዛሬ ይጀመራል - ኢዜአ አማርኛ
የካራባኦ ካፕ የሶስተኛ ዙር መርሐ ግብር ዛሬ ይጀመራል
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 3/2018 (ኢዜአ):- በእንግሊዝ ካራባኦ ካፕ የሶስተኛ ዙር መርሐ ግብር ዛሬ አምስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
ቦርንማውዝ ከሊንከን ሲቲ፣ ሰንደርላንድ ከሁል ሲቲ፣ ክሪስታል ፓላስ ከሚድልስቦሮው እና ሌይተን ኦሪየንት ከብራድፎርድ ሲቲ በተመሳሳይ ምሽት 3 ሰዓት ከ45 ላይ ይጫወታሉ።
ምሽት አራት ሰዓት ላይ ሚልዎል ከኒውካስትል ዩናይትድ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ።
የካራባኦ ካፕ የሶስተኛ ዙር መርሐ ግብር እስከ ቀጣዩ ሳምንት ይቆያል።
እ.አ.አ በ1960 የተጀመረው የካራባኦ ካፕ (በቀድሞ አጠራሩ የእንግሊዝ ፉትቦል ሊግ ዋንጫ) በእንግሊዝ ከአንጋፋው ኤፍ ካፕ ውጪ የሚደረግ ሌላኛው የጥሎ ማለፍ ውድድር ነው።
ሊቨርፑል 10 ጊዜ የካራባኦ ዋንጫን በማንሳት ስኬታማው ክለብ ነው። ማንችስተር ሲቲ ዘጠኝ ጊዜ ውድድሩን በማሸነፍ ይከተላል።
ማንችስተር ዩናይትድ ስድስት ጊዜ እንዲሁም ቼልሲ እና አስቶንቪላ በተመሳሳይ አምስት ጊዜ የዋንጫ ባለቤት ሆነዋል።
ማንችስተር ሲቲ የወቅቱ የውድድሩ አሸናፊ ነው።