ቀጥታ፡

የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዛሬ ይጀመራል

አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 3/2018 (ኢዜአ):- የ2026/27 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሊግ ምዕራፍ (League Phase) ውድድር ዛሬ ጅማሮውን ያደርጋል።

ምሽት አራት ሰዓት ላይ ሪያል ማድሪድ ከኢንተር ሚላን በበርናባው ስታዲየም የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።

ሪያል ማድሪድ 13 ጊዜ ውድድሩን በማሸነፍ ስኬታማው ክለብ ነው። ኢንተር ሚላን ሶስት ጊዜ የዋንጫ ባለቤት ሆኗል።

ሁለቱ ክለቦች በሻምፒዮንስ ሊጉ ከዚህ ቀደም 13 ጊዜ ተገናኝተው ሪያል ማድሪድ በሰባቱ ድል ሲቀናው ኢንተር አምስት ጊዜ አሸንፏል። በቀሪ አንድ ጨዋታ አቻ አቻ ተለያይተዋል።

ለመጨረሻ ጊዜ በውድድሩ ላይ የተገናኙት እ.አ.አ በ2021/22 የውድድር ዓመት ሲሆን በወቅቱ በምድብ ደረጃ ተገናኝተው ሪያል ማድሪድ 2 ለ 0 አሸንፏል።

ጨዋታው ጠንካራ ፉክክር ይታይበታል ተብሎ ይጠበቃል።

ፖርቶ ከማንችስተር ሲቲ፣ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ከቪያሪያል እና ሊል ከሪያል ቤቲስ በተመሳሳይ አራት ሰዓት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ክለብ ብሩዥ ከአስቶንቪላ እና ኤኢኬ አቴንስ ከላስክ በተመሳሳይ ከምሽቱ 1 ሰዓት ከ45 ላይ ይጫወታሉ።

የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሊግ ምዕራፍ (League Phase) ውድድር የመጀመሪያ ጨዋታዎች እስከ ጳጉሜን 5 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም