ቀጥታ፡

በአዲስ አበባ የተከናወኑ የልማት ሥራዎች የሀገሪቱን የማንሰራራት ጉዞ የሚያፋጥኑ ናቸው

አዲስ አበባ ፤ ጳጉሜን 2/2018 (ኢዜአ) ፦ በአዲስ አበባ የተገነቡ የቱሪዝም መዳረሻዎችና ሌሎች የመሠረተ ልማት ሥራዎች የኢትዮጵያን የማንሰራራት ጉዞ የሚያፋጥኑ መሆናቸውን ነዋሪዎች ገለጹ፡፡ 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጳጉሜን 02 "የማንሰራራት ቀን"ን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ የተገነቡ የቱሪዝም መዳረሻዎችንና የመሠረተ ልማት ሥራዎችን ለተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች አስጎብኝቷል።

በጉብኝት መርሃ ግብሩ ላይ የተሳተፉ ጎብኚዎች በአዲስ አበባ የተገነቡ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ከተማዋ ለአፍሪካ ሀገራት ምሳሌ እንድትሆን ያስቻሉ ናቸው ብለዋል፡፡

አስተያየት ሰጪ ሻምበል ዋኘው አባይ እንዳሉትም ከተማዋ ከዚህ ቀደም ከነበራት ገጽታ በተለየ መልኩ ውብና ጽዱ መሆኗን ገልጸው፤ የወንዝ ዳርቻ፣ የኮሪደር ልማትና የቱሪዝም መዳረሻዎች የሀገሪቱን ዕድገት የሚያንሰራሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

አቶ ገዛኸኝ አሰፋ በበኩላቸው የመሠረተ ልማት ሥራዎቹ ለዜጎች የሥራ ዕድል የፈጠሩ፣ ለነዋሪዎችና ለጎብኚዎች ምቹ አካባቢን የፈጠሩ መሆናቸውን በአካል ማረጋገጣቸውን ገልጸዋል፡፡

እነኚህም የኢትዮጵያን የማንሰራራት ግስጋሴ የሚያፋጥኑ ናቸው ብለዋል፡፡ 

የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን በመገናኛ ብዙኃን ከማየት ባለፈ በአካል መጥተው በመጎብኘታቸው መደሰታቸውን የገለጹት ሐጂ ሸምሱ አባስ ፤ የከተማዋ ዕድገት ለሀገር ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቱሪዝም ኮሚሽን ኮሙኒኬሽን ኃላፊ ልደት ሙለታ ጳጉሜን 02 "የማንሰራራት ቀን"ን ምክንያት በማድረግ በለውጡ ዓመታት ለነዋሪዎች ውብና ጽዱ ከተማን ለመፍጠርና በቱሪዝም ዘርፍ የተከናወኑ ሥራዎችን ማስጎብኘታቸውን ገልጸዋል።

ባለፉት ዓመታት የተገነቡ የቱሪዝም መዳረሻዎች፣ የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማት ተግባራት የሀገሪቱን ዕድገት ያረጋገጡ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም