ቀጥታ፡

የመደመር መንግስት በተለያዩ ዘርፎች ያከናወናቸው ተግባራት የኢትዮጵያን ማንሰራራት ለማረጋገጥ ያስቻሉ ናቸው

ደብረማርቆስ፤ ጳጉሜ 2/2018(ኢዜአ)፡- የመደመር መንግስት በተለያዩ ዘርፎች ያከናወናቸው ተግባራት የኢትዮጵያን  ማንሰራራት በተግባር ለማረጋገጥ ያስቻሉ ናቸው ሲል የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።

ከተማ አስተዳደሩ የማንሰራራት  ቀንን አስመልክቶ ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጋር የፓናል ውይይት አካሒዷል።


 

የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ የኋላ ደስታ በዚሁ ወቅት እንደገለፁት፤ የመደመር መንግስት ተግባራዊ ባደረጋቸው የኢንዱስትሪ፣ የከተማ ግብርናና የሰው ተኮር ፕሮጀክቶች ከፍተኛ ስኬቶች ተመዝግበዋል።

ከዚህ ውስጥም በከተማ አስተዳደሩ  ከ10 ዓመት በፊት ከአስር በታች የነበረው  የአምራች ኢንዳስትሪዎች ቁጥር አሁን ላይ ከ70 በላይ ማድረስ የተቻለ ሲሆን 39 የሚሆኑት  ወደ ማምረት የተሸጋገሩ መሆኑን አረጋግጠዋል። 

በማህበራዊ ዘርፍም  በቅድመ አንደኛ ደረጃ፣ በ1ኛና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተደራሽነት፣ ጥራትና አግባብነት ውጤታማ የሆኑ ተግባራት መከናወናቸውን ጠቅሰዋል።

 ከ500 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪም  ሞዴል ትምህርት ቤት ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ መገኘቱ የማንሰራራት ማሳያ እንደሆነም አብራርተዋል።

በስራ እድል ፈጠራ፣ በከተማ ግብርና፣ በመሰረተ ልማት ግንባታና በሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎች አበረታች ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን አስገንዝበዋል። 

ከተሳታፊዎች መካከል ሊቀ ካህናት ይትባረክ መኮነን  እና ወንዳለ ተመስገን እንዳሉት ፤ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በኮሪደርና ሌሎች ልማቶች የታየው  ለውጥ ይበል የሚያሰኝ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል።

በተለይ በከተማ ግብርና ፣ በኢንድስትሪ እና መሰል ስሰራዎች ላይ ያከናወናቸውን ተግባራት ውጤት መምጣቱን ተዘዋውረው መመልከታቸውን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም