ቀጥታ፡

የአርቲስት እልፍነሽ ቀኖ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ነገ በአምቦ ይፈጸማል

አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 2/2018 (ኢዜአ)፦ የአንጋፋዋ አርቲስትና የሰብአዊ መብት ተሟጋች እልፍነሽ ቀኖ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ነገ ጳጉሜን 03 ቀን 2018 ዓ.ም በክብር ሥነ-ሥርዓት ይፈጸማል።


 

አዘጋጅ ኮሚቴው በሰጠው መግለጫ መሠረት፤ የአርቲስቷ አስከሬን ሽኝት ነገ ከጠዋቱ 11:00 እስከ 12:00 ከኮሪያ ሆስፒታል ወደ መኖሪያ ቤቷ የሚደረግ መሆኑን ገልጿል።

ከጠዋቱ 12:00 እስከ 1:00 ባለው ጊዜ ደግሞ አስክሬን ከመኖሪያ ቤቷ ወደ አዲስ አበባ ስታዲየም ይወሰዳል።

የአርቲስቷ ወደጆች ጓደኞችና አድናቂዎችም ነገ ከጠዋቱ 1:00 እስከ 3:00 በአዲስ አበባ ስታዲየም ተገኝተው አሸኛኘት ካደረጉላት በኋላ ወደ አምቦ ሽኝት እንደሚደረግ አዘጋጅ ኮሚቴው ዛሬ በሰጠው መግለጫ ገልጿል።


 

የዕድሜ ልክ ትግሏን ለሰው ልጆች ነፃነትና ለህዝብ ድምፅነት የሰጠችው አርቲስት እልፍነሽ ቀኖ፣ በህይወት እያለች "ከዚህ ዓለም ስሰናበት ቀብሬ አምቦ ይሁን" ባለችው ኑዛዜ መሠረት፣ አስተባባሪ ኮሚቴው የጀግናዋን ፍላጎት በማክበር የመጨረሻ እረፍቷ በአምቦ ከተማ እንዲሆን መወሰኑ ተመላክቷል።

በዜማዎቿ የሕዝብን ብሶትና ተስፋ ስታንጸባርቅ የኖረችው ይህች ታላቅ አርቲስት፣ በግል ሕይወቷም የሁለት ሴቶችና የአንድ ወንድ ልጅ እናት በመሆን መልካም ቤተሰብን ያፈራች እናት ነበረች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም