ቀጥታ፡

የልማት ኃይላችንን ይበልጥ በማፋጠን የኢትዮጵያን ትንሣኤ ወደ ዘላቂ ብልጽግና ከፍ እናደርጋለን - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ ፤ጳጉሜን 2/2018(ኢዜአ)፦ በጀመርነው ታሪካዊ የማንሠራራት ጉዞ የልማት ኃይላችንን ይበልጥ በማፋጠን የኢትዮጵያን ትንሣኤ ወደ ዘላቂ ብልጽግና ከፍ እናደርጋለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የማንሠራራት ቀንን አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ቀደም ሲል “ኢትዮጵያ ተነሥታለች” ሲባል የነበረው ምኞት ሳይሆን ዛሬ በተጨባጭ የተረጋገጠ እውነት መሆኑን ተናግረዋል።

ከታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማማ እስከ ዘመናዊው የኮሪደር ልማት፣ ከቢሾፍቱ ሜጋ አውሮፕላን ማረፊያ እስከ ማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ድረስ ሀገራዊ መነቃቃታችን በተግባር ተመስክሯል ብለዋል።

ይህ ለውጥ በዜጎቻችን የኑሮ ደረጃ፣ በከተሞች መዘመንና የሥራ ዕድል ላይ እውነተኛ ብርሃን ከመሆኑም በላይ ለልጆቻችን የነገ ብሩህ ተስፋን የሚሰንቅ ታላቅ ርዕይ ነው ሲሉም ገልጸዋል።

ከእንግዲህ ወደኋላ አንመለስም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጀመርነው ታሪካዊ የማንሠራራት ጉዞ የልማት ኃይላችንን ይበልጥ በማፋጠን የኢትዮጵያን ትንሣኤ ወደ ዘላቂ ብልጽግና ከፍ እናደርጋለን ብለዋል።

#EthiopiaDelivers

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም