የግብርና ልማትን ጨምሮ በቱሪዝም፣ ኢንዱስትሪና የማዕድን ዘርፎች የተመዘገበው ስኬት የኢትዮጵያን እመርታና ብሩህ ተስፋ የሚያመላክት ነው - ኢዜአ አማርኛ
የግብርና ልማትን ጨምሮ በቱሪዝም፣ ኢንዱስትሪና የማዕድን ዘርፎች የተመዘገበው ስኬት የኢትዮጵያን እመርታና ብሩህ ተስፋ የሚያመላክት ነው
ሐረማያ፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡- የግብርና ልማትን ጨምሮ በቱሪዝም፣ ኢንዱስትሪና የማዕድን ዘርፎች የተመዘገበው ስኬት የኢትዮጵያን እመርታና ብሩህ ተስፋ የሚያመላክት መሆኑን በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የግብርና ምጣኔ ሃብት ተባባሪ ፕሮፌሰር ከተማ በቀለ (ዶ/ር) ገለጹ።
በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የግብርና ምጣኔ ሃብት ተባባሪ ፕሮፌሰር ከተማ በቀለ (ዶ/ር)፤ የኢትዮጵያ ብዝሃ የኢኮኖሚ አማራጮች ቀጣይነት ያለው እድገትና ስኬት የሚያመጡ ስለመሆናቸው አብራርተዋል።
ባለፉት ጥቂት ዓመታት የግብር ልማትን ጨምሮ በቱሪዝም፣ ኢንዱስትሪ፣ የማዕድን ዘርፍ እና በዲጅታላይዜሽን የተከናወኑ ተግባራት የላቀ ውጤት የተገኘባቸው መሆኑን አንስተዋል።
የግብርናው ዘርፍ አገሪቷ ያላትን የስው ሃይል፣ ውሃ፣መሬትና ሌሎች ሃብትን ባግባቡ በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ረገድ የሚታይና የሚጨበጥ ውጤት መገኘቱን ጠቅሰዋል።
በተለይም ደግሞ የስንዴ ልማት በኢትዮጵያ አዲስ ታሪክ የተሰራበት መሆኑን ጠቅሰው ምርታማነትን በማሳደግ ከተረጅነት የመውጣት ጥረት በጥሩ መንገድ ላይ ስለመሆኑ አስረድተዋል።
የቱሪዝም፣ የማዕድን እና የአይ ሲቲ ሴክተሮችም ኢትዮጵያን ወደ ፊት እያራመዱ ያሉ ስለመሆናቸው አብራርተዋል።
በኢንዱስትሪው ዘርፍ በተለይ ደግሞ በኢትዮጵያ ታምርት በመታገዝ ምርታማነትን በማሳደግ ለወጪ ንግድና ለሀገር ውስጥ ፍጆታ በመጠቀም ስኬት ስለመመዝገቡ አንስተዋል።
የኢንዱስትሪ ዘርፉ ለበርካታ ዜጎች የስራ እድልና የቴክኖሎጂ ሽግግር ከማበርከት ባለፈ የውጭ ምንዛሬን በማዳን ረገድ ትርጉም ያለው ውጤት አምጥቷል ብለዋል።
በድምሩ የግብርና ልማትን ጨምሮ በቱሪዝም፣ ኢንዱስትሪና የማዕድን ዘርፎች የተመዘገበው ስኬት የኢትዮጵያን እመርታና ብሩህ ተስፋ የሚያመላክት መሆኑን ገልጸዋል።