የክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የኃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች የደብረ ማርቆስ ጉብኝት - ኢዜአ አማርኛ
የክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የኃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች የደብረ ማርቆስ ጉብኝት
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 30/2018 (ኢዜአ) ፦ የክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የኃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች የደብረ ማርቆስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ጨምሮ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ።
የሰላም ሚኒስቴር ሀገር በቀል ዕውቀትና ባህላዊ ሀብቶች ለሰላም ግንባታ ያላቸውን ሚና በተመለከተ ከክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የኃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የጸጥታ አካላት ጋር በደብረ ማርቆስ ከተማ ውይይት አድርገዋል።
የኃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ከልምድ ልውውጥና ውይይቱ ባለፈ በከተማዋ የተሠሩ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።
የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን የግንባታ ሂደት ተመልክተዋል።
የኃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች የኮሪደር ልማት ሥራዎችን፣ በመጠናቀቅ ላይ ያለውን የደብረ ማርቆስ ጠቅላላ ሆስፒታል፣ የአማራ ልማት ማህበር (አልማ) ሕንፃ ግንባታ እና ሌሎች የልማት ሥራዎችንም ጎብኝተዋል።