የአየር መንገዱ ሰራተኞች በአዲስ አበባ የተለያዩ የቱሪዝም መዳረሻዎች እና የወንዝ ዳርቻ ልማትን ጎበኙ - ኢዜአ አማርኛ
የአየር መንገዱ ሰራተኞች በአዲስ አበባ የተለያዩ የቱሪዝም መዳረሻዎች እና የወንዝ ዳርቻ ልማትን ጎበኙ
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 30/2018 (ኢዜአ):- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች በአዲስ አበባ የተለያዩ የቱሪዝም መዳረሻዎች እና የወንዝ ዳርቻ ልማትን ጎብኝተዋል።
ሰራተኞቹ ከእንጦጦ እስከ ፒኮክ ፓርክ ድረስ የተሰሩትን የወንዝ ዳርቻ ልማትን ተመልክተዋል።
እንዲሁም የመዲናዋን አዲስ ገጽታና የቱሪዝም ሳቢነት የሚያጎሉ የመሰረተ ልማት እና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችንም ጎብኝተዋል።
በጉብኝታቸውም በመዲናዋ የተከናወኑት የልማት ስራዎች እጅግ የሚደነቁ መሆናቸውን ገልጸው፤ አዲስ አበባን የአፍሪካ የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የተጀመረውን ሁሉን አቀፍ የልማት ስራ እንደሚደግፉ እና የድርሻቸውን ለመወጣት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።
የአዲስ በባ ቱሪዝም ኮሚሽን በከተማዋ የሚገኙ የተለያዩ ተቋማት ሰራተኞች በመዲናዋ የለሙትን የቱሪዝም መዳረሻዎች እንዲጎበኙ በርካታ የማስተዋወቅ ስራን እያከናወነ እንደሚገኝ የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።