ኒውካስትል ዩናይትድ እና ቦርንማውዝ አቻ ተለያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ኒውካስትል ዩናይትድ እና ቦርንማውዝ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 30/2018 (ኢዜአ):- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሶስተኛ ሳምንት ጨዋታ ኒውካስትል ዩናይትድ እና ቦርንማውዝ ያደረጉት ጨዋታ ሁለት አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል።
በሴንት ጀምስ ፓርክ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሃርቪ ባርንስ እና ጃኮብ ራምሴ ለኒውካስትል ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ማርከስ ታቫርኒየር እና የኒውካስትሉ ተከላካይ ማሊክጅ ቲያው በራሱ ላይ የቦርንማውዝን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ጃኮብ ራምሴ በ88ኛው ደቂቃ ያስቆጠረው ጎል ኒውካስትልን አቻ አድርጓል።
ቦርንማውዝ በጨዋታው 2 ለ 0 መምራት ቢችልም ውጤቱን ማስጠበቅ አልቻለም።
በመጀመሪያው አጋማሽ ቦርንማውዝ፣ በሁለተኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ኒውካስትል ብልጫ ወስደው ተጫውተዋል።
ውጤቱን ተከትሎ ኒውካስትል በአምስት ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዟል።
ቦርንማውዝ በበኩሉ በሁለት ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ቡድኑ እስከ አሁን በሊጉ ምንም ጨዋታ አላሸነፈም።