በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ሽንፈት አስተናገደ - ኢዜአ አማርኛ
በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ሽንፈት አስተናገደ
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ):- በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የመጀመሪያ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በሱዳኑ ሂላል አል-ሳሂል 2 ለ 1 ተሸንፏል።
ማምሻውን በሩዋንዳ በሚገኘው ኪጋሊ ፔሌ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዋሊድ አል-ሻላ እና ፋሪስ ሞሂ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ካርሎስ ዳምጠው ለወልዋሎ ጎሏን ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከሜዳው ውጪ ወሳኝ ጎል አስቆጥሯል።
የሁለቱ ክለቦች የመልስ ጨዋታ መስከረም 2 ቀን 2019 ዓ.ም በድሬዳዋ ስታዲየም ይካሄዳል።
ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በደርሶ መልስ ውጤት ካሸነፈ በሁለተኛ ዙር ከዛንዚባሩ ኬኤምኬኤም እና ከሊቢያው አል አህሊ ትሪፖሊ አሸናፊ ጋር የሚጫወት ይሆናል።
ቡድኑ በአህጉራዊው መድረክ ለመሳተፍ የበቃው በኢትዮጵያ ዋንጫ ፍጻሜ ሲዳማ ቡናን 2 ለ 0 አሸንፎ ሻምፒዮን መሆኑን ተከትሎ ነው።
ወልዋሎ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ሲሳተፍ በክለቡ የ70 ዓመታት ታሪክ የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።