ቀጥታ፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ(ዶ/ር) ከአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ፀሃፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ) ፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (/) የአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሲያን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ሁለቱ ወገኖች በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል ያለውን የቆየ የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ መክረዋል።

የሀገራቱን የኢንቨስትመንት እና የንግድ ትስስርን ማጠናከር ላይም የተወያዩ ሲሆን የጋራ ፍላጎታቸው በሆኑ ቀጣናዊ የሰላም እና ጸጥታ ጉዳዮች ላይ ሃሳቦችን ተለዋውጠዋል።


 

ኢትዮጵያና አሜሪካ በግንቦት ወር 2018 .. በዋሽንግተን .. በኢኮኖሚ ብልጽግና፣ በንግድና ኢንቨስትመንት፤ በመከላከያ እና ጸጥታ ትብብር፤ እንዲሁም ቀጣናዊ ሰላም እና መረጋጋትን በማስፈን ዙሪያ የሁለትዮሽ ውይይት ማካሄዳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመረጃው አውስቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም