ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ):- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ የእንኳን ደስ አልዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የጣልያን መንግሥት ታሪካዊ ምዕራፍ ላይ መድረሱን አስመልክቶ ለአስተዳደሩ እና ለጣልያን ሕዝብ የተሰማቸውን ልባዊ የደስታ መግለጫ አቅርበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ጣልያን በጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ጠንካራ እና አርቆ አሳቢ መሪነት በዘመናዊቷ የጣሊያን ሪፐብሊክ ታሪክ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ መረጋጋትን ማስፈኑን አመልክተዋል።
የሜሎኒ ጽናትና ቀጣይነት ያለው ትጋት ዓለም አቀፍ መነሳሳትን ከመፍጠሩም ባሻገር፣ በኢትዮጵያ እና በጣልያን መካከል የቆየውን ሁሉን አቀፍ እና ጥልቅ ትብብር ይበልጥ ማጠናከሩን ገልጸዋል።
ሁለቱ ሀገራት በመከባበር ላይ ለተመሰረተው የጋራ ትብብራቸው ከፍተኛ ዋጋ እንደሚሰጡ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለጣልያን መንግሥትና ሕዝብ ዘላቂ ሰላም እና ብልጽግናን ተመኝተዋል።