ፓርቲው የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትጋት ይሰራል-አቶ ጌቱ ወዬሳ - ኢዜአ አማርኛ
ፓርቲው የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትጋት ይሰራል-አቶ ጌቱ ወዬሳ
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 26/2018 ( ኢዜአ)፦ብልፅግና ፓርቲ የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትጋት እንደሚሰራ በብልፅግና ፓርቲ የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ ገለፁ።
የጽህፈት ቤቱ ኃላፊው አቶ ጌቱ ወዬሳ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት በክልሉ በብልፅግና ፓርቲ መሪነት በተለያዩ ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት በርካታ ስኬቶች ተመዝግበዋል።
የፓርቲውን እሳቤዎች በተግባር በመተርጎም በየዘርፉ የተመዘገቡ ድሎችን አጠናክሮ ማስቀጠል ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።
በያዝነው አዲሱ የበጀት ዓመትም ፓርቲው ለህዝብ የገባውን ቃል አልቆ የሚፈፅምበትና እንደሀገርና ክልል አዲስ ታሪካዊ ምዕራፍ የሚከፈትበት እንዲሆን በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
የብልፅግና ፓርቲ እሳቤዎች እና የፖለቲካ ፕሮግራሞች ወደ ተግባር በመቀየር የህዝባችንን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ነው ያነሱት።
እነኚህ ድሎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉም በተለይ በአገልግሎት አሰጣጥ የህዝብን እርካታ ማሳደግ እንዲሁም ብልሹ አሰራሮችን ከማስወገድ አንፃር በልዩ ትኩረት መንቀሳቀስ አስፈላጊ ነው ብለዋሎል።
በፓርቲና በመንግሥት የተቀናጀ አመራር የስራ ዕድል ፈጠራን ለማስፋት፣ገበያን የማረጋጋትና የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ የጀመራቸው ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።
የፓርቲ አደረጃጀቶችና አባላት በዘርፉ ግንባር ቀደም ሚና ሊጫወቱ እንደሚገባ በማሳሰብ፣ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰሩ ያሉ ስራዎች መቀጠል እንዳለበት አመልክተዋል።
የሴቶችና ወጣቶች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንዲሁም የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት የሚያሳድጉ ስራዎችን በማላቅ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ እና ልመናንና ተረጂነትን ለመቀነስ ይሰራል ሲሉ አብራርተዋል።
"አዲሱ በጀት ዓመት ህዝባችንን ይበልጥ የምናገለግልበት፣ ክልሉን የብልፅግና ተምሳሌት የማድረግ ጉዟችንን የምናረጋግጥበት እንዲሆን ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ይደረጋል''።
የ2019 በጀት ዓመት ዕቅዶች በተሻለ አፈጻጸም እንዲተገበሩ ሁሉም የፓርቲ መዋቅሮችና የመንግሥት ተቋማት በቅንጅት፣ በተጠያቂነትና በውጤት ተኮር አሰራር ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባም ጠቁመዋል።
የታቀዱ ግቦችን ለማሳካት በየደረጃው የሚገኘው አመራር በቁርጠኝነትና በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት መስራት እንደሚገባውም አጽንኦት ሰጥተዋል።