የብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን "በብዝሐነት የደመቀች፣በምክክር የጸናች ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል ይከበራል - ኢዜአ አማርኛ
የብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን "በብዝሐነት የደመቀች፣በምክክር የጸናች ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል ይከበራል
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 26/2018 (ኢዜአ)፦ 21ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን "በብዝሐነት የደመቀች፣ በምክክር የጸናች ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ሐሳብ በደማቅ ሁኔታ እንዲከበር ተወሰነ።
ውሳኔው የተላለፈው የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር፣ የክልሎችና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች አፈ-ጉባዔዎች፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የበዓሉን ረቂቅ ዕቅድ ለማጽደቅ በተካሄደ የምክክር መድረክ ላይ ነው።
በመድረኩ እንደተመላከተው፤በዓሉ የተመረጠውን መሪ ሐሳብ መሠረት በማድረግ የሕዝቦችን አንድነት በሚያጠናክር፣ብዝሐነትን በሚያጎላና የምክክር ባህልን በሚያዳብር መልኩ ይከበራል።
በዓሉን በታቀደው መሠረት በደማቅ ሁኔታ ለማክበር የሚያስችሉ አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅቶች በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኙም ተገልጿል።