ቀጥታ፡

የአማራ ክልልን ሰላምና ጸጥታ ለማስጠበቅና ልማትን ለማስቀጠል የሚደረጉ ቅንጅታዊ ጥረቶች ተጠናክረው ይቀጥላሉ - ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ባህርዳር ፤ ነሀሴ 25/2018 (ኢዜአ) ፦የአማራ ክልልን  ሰላምና ጸጥታ ለማስጠበቅና ልማትን ለማስቀጠል የሚደረጉ ቅንጅታዊ ጥረቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ገለጹ።

የ2018 በጀት ዓመት የፓርቲ እና የመንግስት ሥራ አፈጻጸም እንዲሁም የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ ላይ ያተኮረ መድረክ የክልሉ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በተገኙበት እየተካሄደ ነው።


 

በመድረኩ ላይ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ እንደተናገሩት የክልሉን ሰላምና ጸጥታን ለማስጠበቅና ልማት ለማሳለጥ የሚደረጉ ቅንጅታዊ ጥረቶች ተጠናክረው ይቀጥላሉ።

ለዚህም በየደረጃው ያሉ አመራሮች ህብረተሰቡን በማሳተፍ የላቀ ሚናቸውን ይበልጥ እንዲወጡ አስገንዝበዋል።

አመራሩ ህዝብን በቁርጠኝነት በማገልገል በትብብር የተጀመሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል ከዳር ማድረስ አለበት ሲሉ አሳስበዋል።

የክልሉ ሕዝብ ከመንግስት ጎን ሆኖ ጽንፈኞችን በመዋጋት በልማትና በሌሎች ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በንቃት እየተሳተፈ መሆኑንም አንስተዋል።

በቀጣይም የክልሉን ሕዝብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ ከመቼውም ጊዜ በላይ በቅንጅት እንደሚሰራ ርዕሰ መስተዳድሩ አጽኖት ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም