ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሴካፋ ማጣሪያ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቀቀ

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 25/2018 (ኢዜአ)፦ በካፍ የሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ የደረጃ ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደቡብ ሱዳኑን ዬ ጆይንት ስታርስን 6 ለ 1 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል።

በኪጋሊ ፔሌ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ እፀገነት ግርማ፣ ብዙአየሁ ታደሰ፣ ማህሌት ምትኩ፣ እሙሽ ዳንኤል፣ ምህረት አየለ እና ረድኤት አስረሳኸኝ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ማውሪን ናንኪንጋ በፍጹም ቅጣት ምት የዬ ጆይንት ስታርስን የማስተዛዘኛ ጎል ከመረብ ላይ አሳርፋለች።

ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በማጣሪያው ሶስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።

ንግድ ባንክ በግማሽ ፍጻሜው በዩጋንዳው ካዌምፔ ሙስሊም ሌዲስ መሸነፉን ተከትሎ በካፍ ሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ የመሳተፍ ህልሙ ማክተሙ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም