የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ተጋጣሚዎቹን አውቋል - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ተጋጣሚዎቹን አውቋል
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 25/2018 (ኢዜአ)፦ ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ውድድር የዕጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ዛሬ በሩዋንዳ ኪጋሊ ተካሄዷል።
በሴካፋ ዞን የምትገኘው ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከአዘጋጇ ታንዛንያና ሩዋንዳ ጋር ተደልድላለች።
ዩጋንዳ፣ ሱዳን እና ጅቡቲ በምድብ ሁለት የሚገኙ ሀገራት ናቸው። በምድብ ሶስት ደቡብ ሱዳን፣ ኬንያና ብሩንዲ ተደልድለዋል።
ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ውድድር ከመስከረም 6 እስከ 20 ቀን 2019 ዓ.ም ይካሄዳል።
በውድድሩ ላይ አንደኛና ሁለተኛ የሚወጡ ሀገራት እ.አ.አ በ2027 በጋና በሚካሄደው ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ዞኑን ወክለው ይሳተፋሉ።
በስድስት አህጉራዊ ዞኖች በሚካሄዱት የማጣሪያ ውድድሮች በእያንዳንዱ ቀጣና ሁለት ሀገራት ለአፍሪካ ዋንጫው ያልፋሉ።