ቀጥታ፡

ማንችስተር ዩናይትድ በብሩኖ ፈርናንዴዝ ሀትሪክ ታግዞ በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን አስመዘገበ

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት ጨዋታ ማንችስተር ዩናይትድ ኤፕስዊች ታውንን 5 ለ 2 ረትቷል።

ማምሻውን በኦልትራፎርድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ብሩኖ ፈርናንዴዝ ሶስት ግቦችን (አንድ በፍጹም ቅጣት ምት) በማስቆጠር ሀትሪክ ሰርቷል።

የ31 ዓመቱ አማካይ በአዲሱ የውድድር ዓመት ሀትሪክ የሰራ የመጀመሪያ ተጫዋች ሆኗል።

ብሪያን ምቡሞ እና የኤፕስዊቹ ጃኮብ ግሪቭስ በራሱ ላይ ቀሪዎቹን ጎሎች ለማንችስተር ዩናይትድ ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ሀትሪክ የሰራው ፈርናንዴዝ ለሙቤሞ ጎል ኳስ አመቻችቶ አቀብሏል።የጨዋታው ኮከብ በመባልም ተመርጧል።

ሌፍ ዴቪስ እና ቹባ አክፖም የኤፕስዊችን ጎሎች ከመረብ ጋር አገናኝተዋል።

በመጀመሪያው አጋማሽ ብልጫ ተወስዶበት የነበረው ማንችስተር ዩናይትድ በሁለተኛው አጋማሽ ፍጹም የበላይነት ወስዶ ተጫውቷል።

ውጤቱን ተከትሎ ዩናይትድ በሊጉ የመጀመሪያ ድሉን አግኝቷል።

አዲስ አዳጊው ኤፕስዊች ታውን በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ሽንፈቱን አስተናግዷል።

በሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ ከኤቨርተን፣ ኤፕስዊች ታውን ከሊቨርፑል ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም