ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኖርዌይ ንጉሥ ሃራልድ 5ኛ ኅልፈት የተሰማቸውን ኀዘን ገለጹ

አዲስ አበባ ፤ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኖርዌይ ንጉሥ ሃራልድ 5ኛ ኅልፈት የተሰማቸውን ኀዘን ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በንጉሥ ሃራልድ 5ኛ ኅልፈት የተሰማቸውን ኀዘን በኢትዮጵያ መንግሥት እና ሕዝብ ስም የገለፁ ሲሆን ኖርዌይም የኢትዮጵያ አስተማማኝ አጋር ነች ብለዋል::

በዚህ የሐዘን ወቅትም የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ከኖርዌይ ሕዝብ ጎን እንደሚቆም ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም