ቀጥታ፡

ቼልሲ ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቼልሲ ብራይተንን 4 ለ 3 ረትቷል።

በስታምፎርድ ብሪጅ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሮሚዮ ላቪያ፣ ፔድሮ ኔቶ፣ ጆአኦ ፔድሮ እና ኮል ፓልመር ለሰማያዊዎቹ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ማሊክ ያልኩዬ፣ ፓስካል ግሮስ እና የቼልሲው ጆአኦ ፔድሮ በራሱ ላይ የብራይተንን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ባለሜዳው ቼልሲ የበላይነት ወስዶ ተጫውቷል።

ጨዋታው በርካታ የግብ እድሎች የተፈጠሩበት ነበር።

ብራይተን በሁለተኛው አጋማሽ ወደ ጨዋታው ለመመለስ ያደረገው ጥረት አልተሳካም።

ተቀይሮ የገባው የቼልሲው ሞሰስ ካይሴዶ ጉዳት አጋጥሞት ተቀይሮ ወጥቷል።

የምዕራብ ለንደኑ ቼልሲ በሊጉ ተከታታይ ድሉን አስመዝግቧል።

በአንጻሩ ብራይተን የውድድር ዓመቱን የመጀመሪያ ሽንፈት አስተናግዷል።




በስታዲየም ኦፍ ላይት በተደረገው ጨዋታ ሰንደርላንድ ፉልሃምን 1 ለ 0 አሸንፏል።

ዊልሰን ኢሲዶር በ75ኛው ደቂቃ ጎሉን ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ሰንደላንድ በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ሶስት ነጥቡን ወደ ካዝናው አስገብቷል።

የለንደኑ ፉልሃም ተከታታይ ሽንፈቱን አስተናግዷል።




በሌላኛው መርሐ ግብር ሊድስ ዩናይትድ እና ብሬንትፎርድ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

በኢላንድ ሮድ በተካሄደው ጨዋታ ዶምኒክ ካልቨርት-ሉዊን ለሊድስ እና ኬቨን ሻደ ለብሬንትፎርድ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

በመጀመሪያ የሊግ  ጨዋታቸው ያሸነፉት ሁለቱ ክለቦች አንድ ነጥብ አሳክተዋል።

ምሽት 12 ሰዓት ከ30 ማንችስተር ዩናይትድ ከኤፕስዊች ታውን በኦልድትራፎርድ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም