ቀጥታ፡

በሐረሪ ክልል በመደመር መንግሥት ዕይታ የግብርናው ዘርፍ ምርትና ምርታማነት እመርታዊ ለውጥ

በሐረሪ ክልል በመደመር መንግሥት ዕይታ በግብርናው ዘርፍ ምርትና ምርታማነት እመርታዊ ለውጥ ተመዝግቧል።

በመደመር መንግሥት ዕይታ በግብርናው ዘርፍ ገበያ ተኮር ምርቶችን በዓይነት፣ በምርት ብዛትና በጥራት የማምረት እመርታዊ ለውጥ መመዝገቡን ተችሏል።

በዚህም የተቀናጀ የግብርና ስራ የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት በማሳደግ ተጨባጭ ስኬቶች ተመዝግበዋል።


 

በክልሉ ባለፉት ዓመታት በሰብል፣በአትክልትና ፍራፍሬ፣ በእንስሳት ሀብት ልማት፣ በሌማት ትሩፋትና በተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ላይ ውጤታማ ስራዎች ተከናውነዋል።

በክልሉ ከተማና ገጠር ወረዳዎች በሌማት ትሩፋት መርሃግብር የእንስሳት ተዋጽኦና የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት አበረታች ስራዎች ተሰርቷል።

በተለይም በገጠር ወረዳዎች በመስኖ ልማት የተከናወኑ ስራዎች ምርትና ምርታማነት እንዲጎለብትና የአርሶ አደሩ የምግብ ዋስትና እንዲረጋገጥ ከማስቻል ባለፈ ለገበያ አቅርቦት ከፍተኛ እገዛ እያደረጉ ይገኛሉ።


 

በሰብል ልማት በየተከናወኑ ተግባራትም አርሶ አደሩን ከተረጂነት ወደ ምርታማነት እያሸጋገሩ የሚገኙ ውጤት መመዝገብ ተችሏል።

በተለይም በክልሉ የዝናብ እጥረትና በሽታን በመቋቋም በአጭር ጊዜ ምርት የተቀናጀ የግብርና ስራ የሚሰጡ የማሽላና በቆሎ ሰብሎች ምርት እና ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል።


 

በቀጣይም የተቀናጀ የግብርና ስራን በማጠናከር የአርሶ አደሩን ምርታማነት የሚያሳድጉ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም