ቀጥታ፡

አዲሱ ጎበና የሲድኒ ማራቶን የስፍራውን ክብረወሰን በማሻሻል አሸነፈ

አዲስ አበባ ፤ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፦በዓለም አትሌቲክስ የሜጀር ደረጃ በተሰጠው የሲድኒ ማራቶን በኢትዮጵያዊው አትሌት አዲሱ ጎበና አሸናፊነት ተጠናቋል።

ለ24ኛ ጊዜ በተካሄደው በዚህ ውድድር አዲሱ ጎበና ርቀቱን 2 ሰዓት 04 ደቂቃ ከ42 ሴኮንድ በሆነ ፈጣን ሰዓት በማጠናቀቅ የቦታውን አዲስ ክብረወሰን አስመዝግቧል።

አትሌቱ ባለፈው ዓመት በተካሄደው የሲድኒ ማራቶን 2ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ የሚታወስ ሲሆን፣ ዘንድሮ ግን የቦታውን ክብረወሰን ከአንድ ደቂቃ በላይ አሻሽሏል።

አትሌት ጭምዴሳ ደበሌ 2:04:46 በሆነ ጊዜ 2ኛ ደረጃን ይዞ ሲያጠናቅቅ፣ ጀማል መኮንን 5ኛ ደረጃን አግኝቷል።

የባለፈው ዓመት አሸናፊና የቦታው ክብረወሰን ባለቤት የነበረው ኃይለማሪያም ኪሮስ 6ኛ ዳዊት ወልዴ 8ኛ ወጥተዋል።

በሴቶች ኬንያዊቷ አትሌት ፔሬስ ጄፕቺርቺር በ2:18:31 በማጠናቀቅ ቀዳሚ ሆናለች።

ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች ሹሬ ደምሴ፣ ሄቨን ኃይሉ እና መሰረት አበባየሁ ከ3ኛ እስከ 5ኛ ያሉትን ደረጃዎች በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም