የፕሪሚየር ሊጉ ተጠባቂ መርሐ ግብሮች፡ ማንችስተር ዩናይትድ ከኢፕስዊች ታውን፣ ቼልሲ ከብራይተን - ኢዜአ አማርኛ
የፕሪሚየር ሊጉ ተጠባቂ መርሐ ግብሮች፡ ማንችስተር ዩናይትድ ከኢፕስዊች ታውን፣ ቼልሲ ከብራይተን
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፦ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬም ቀጥለው ይካሄዳሉ።
በዕለቱ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
ከመርሐ ግብሮቹ መካከል ማንችስተር ዩናይትድ ከኤፕስዊች ታውን ምሽት 12 ሰዓት ከ30 ላይ በኦልትራፎርድ ስታዲየም የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠቃሽ ነው።
ዩናይትድ በመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብር ባልተጠበቀ ሁኔታ በአዲስ አዳጊው ሁል ሲቲ 2 ለ 0 ተሸንፏል።
በአንጻሩ አዲስ አዳጊው ኤፕስዊች ታውን ሰንደርላንድን 2 ለ 1 በማሸነፍ ዓመቱን በድል ጀምሯል።
ማንችስተር ዩናይትድ አሁንም ከአዲስ አዳጊ ክለብ ጋር ተገናኝቷል። ቡድኑ የመጀመሪያ ድሉን ለማግኘት ይጫወታል።
ኤፕስዊች ታውን ተከታታይ ድሉን ለማስመዝገብ ጠንካራ ፍልሚያ ይጠብቀዋል።
በሌላኛው መርሐ ግብር ቼልሲ ብራይተንን ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ በስታምፎርድ ብሪጅ ስታዲየም ያስተናግዳል።
የምዕራብ ለንደኑ ቼልሲ በመጀመሪያው ጨዋታው ከሜዳው ውጪ ፉልሃምን 2 ለ 1 ረቷል።
የምስራቅ ኤሴክሱ ብራይተን አስቶንቪላን 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል።
በመጀመሪያ መርሐ ግብራቸው ድንቅ የማጥቃት እንቅስቃሴ ያሳዩት ሁለቱ ቡድኖች ዛሬም ማራኪ ጨዋታ ለተመልካች እንደሚያሳዩ ይጠበቃል።
ሊድስ ዩናይትድ ከብሬንትፎርድ፣ ሰንደርላንድ ከፉልሃም በተመሳሳይ 10 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።