ቶተንሃም ሆትስፐርስ ተከታታይ ሽንፈት አስተናገደ - ኢዜአ አማርኛ
ቶተንሃም ሆትስፐርስ ተከታታይ ሽንፈት አስተናገደ
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 23/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኒውካስትል ዩናይትድ ቶተንሃም ሆትስፐርስን 2 ለ 0 አሸንፏል።
ማምሻውን በቶተንሃም ሆትስፐርስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አንቶኒ ኢላንጋ እና ዮአን ዊሳ የማሸነፊዬ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ኒውካስትል ዩናይትድ ያገኛቸውን የግብ እድሎች በሚገባ መጠቀሙ አሸናፊ አድርጎታል።
ባለሜዳው ቶተንሃም የጨዋታ ብልጫ ቢወስድም ኢላማቸውን የጠበቁ ሙከራዎችን ማድረግ ላይ ተቸግሮ ታይቷል።
ውጤቱን ተከትሎ ኒውካስትል የውድድር ዓመቱን የመጀመሪያ ሶስት ነጥብ አግኝቷል።
አዲሱ ጀርመናዊ አሰልጣኝ ማቲያስ ጃይስል የመጀመሪያ ድላቸውን አግኝተዋል።
በአንጻሩ ቶተንሃም ሆትስፐርስ ተከታታይ ሽንፈቱን አስተናግዷል።
በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት በርካታ ገንዘብ ያወጣው የሮቤርቶ ዲዘርቢው ቶተንሃም ደካማ አጀማመር አሳይቷል።
በሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቶተንሃም ሆትስፐርስ ከኖቲንግሃም ፎረስት፣ ኒውካስትል ዩናይትድ ከቦርንማውዝ ይጫወታሉ።