በሶማሌ ክልል የመሰረተ ልማት ግንባታ ስራዎች በተቀናጀ መልኩ እየተከናወኑ ነው - ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሁመድ - ኢዜአ አማርኛ
በሶማሌ ክልል የመሰረተ ልማት ግንባታ ስራዎች በተቀናጀ መልኩ እየተከናወኑ ነው - ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሁመድ
ጅግጅጋ፤ ነሐሴ 23/2018 (ኢዜአ)፦ በሶማሌ ክልል የተቋማትና የመሰረተ ልማት ግንባታ ስራዎች በተቀናጀ መልኩ እየተከናወኑ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሁመድ ገለጹ።
ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ፤ የክልሉን ኢንቨስትመንትና የኢንዱስትሪና ቢሮ አዲስና ዘመናዊ የህንፃ ግንባታ አስጀምረዋል።
በዚሁ መርሃ ግብር ላይ ባደረጉት ንግግርም በክልሉ የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ሁለንተናዊ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል።
ከልማት ስራዎች በተጓዳኝ የመንግስት አገልግሎቶችን ምቹ፣ ፈጣንና ቀልጣፋ የማድረግ ጥረት ተጠናክሮ መቀጠሉን አንስተዋል።
በዛሬው እለትም የክልሉን ኢንቨስትመንትና የኢንዱስትሪና ቢሮ አዲስና ዘመናዊ የህንፃ ግንባታ መጀመሩን ገልጸው፤ የተቋማትና የመሰረተ ልማት ግንባታ ስራዎች ይቀጥላሉ ብለዋል።
ከዚህ ጎን ለጎን የትምህርት፣ የውሃ፣ የመንገድ፣ የጤና የዲጂታል ልማትና ሌሎችም ስራዎች በልዩ ትኩረት እየተከናወኑ መሆኑንም ገልጸዋል።
በክልሉ ከተሞችም ይሁን በገጠር ሰው ተኮር የሆኑ ልማቶችን የመገንባትና የዜጎችን ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ስራ ዋነኛ ትኩረታችን ሆኖ ይቀጥላል ብለዋል።