አዲስ አዳጊው ሁል ሲቲ ተከታታይ ድሉን ሲያስመዘግብ ቦርንማውዝ እና ኤቨርተን አቻ ተለያይተዋል - ኢዜአ አማርኛ
አዲስ አዳጊው ሁል ሲቲ ተከታታይ ድሉን ሲያስመዘግብ ቦርንማውዝ እና ኤቨርተን አቻ ተለያይተዋል
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 23/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬም መካሄዱን ቀጥሏል።
በኮቨንተሪ ቢውልዲንግ ሶሳይቲ አሬና በተካሄደው ጨዋታ ሁል ሲቲ ኮቨንተሪ ሲቲን 1 ለ 0 አሸንፏል።
ሊያም ሚላር በ82ኛው ደቂቃ ግቧን አስቆጥሯል።
ውጤቱን ተከትሎ አዲስ አዳጊው ሁልሲቲ ተከታታይ ድሉን በማስመዝገብ ያልተጠበቀ ጅማሮ አድርጓል።
በአንጻሩ ሌላኛው አዳጊ ክለብ ኮቨንተሪ ሲቲ ተከታታይ የሊግ ሽንፈቱን አስተናግዷል።
በቫይታሊቲ ስታዲየም በተካሄደው ሌላኛው መርሐ ግብር ቦርንማውዝ እና ኤቨርተን አንድ አቻ ተለያይተዋል።
አሌክስ ስኮት ለቦርንማውዝ፣ ጀምስ ታርኮስኪ ለኤቨርተን ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ታርኮስኪ በ91ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፋት ጎል ኤቨርተንን አቻ አድርጋለች።
በመጀመሪያ የሊግ ጨዋታቸው ሽንፈት ያስተናገዱት ሁለቱ ክለቦች የመጀመሪያ ነጥባቸውን አግኝተዋል።
ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ ቶተንሃም ሆትስፐርስ ከኒውካስትል ዩናይትድ በቶተንሃም ሆትስፐርስ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ቀን ላይ በተካሄደ ጨዋታ ሊቨርፑል እና ኖቶንግሃም ፎረስት ሁለት አቻ ተለያይተዋል።