ቀጥታ፡

ሊቨርፑል እና ኖቲንግሃም ፎረስት አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 23/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሊቨርፑል እና ኖቲግሃም ፎረስት ያደረጉት ጨዋታ ሁለት አቻ ተጠናቋል።

በአንፊልድ ሮድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አሌክሳንደር ኢሳቅ እና ቪክቶር ሙኞዝ ለሊቨርፑል ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ዳን ንዶይ እና ሞርጋን ጊብስ-ዋይት (ፍጹም ቅጣት ምት) ለፎረስት ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ጨዋታው ተመጣጣኝ እና አዝናኝ ፉክክር ተደርጎበታል።

ኖቲንግሃም ፎረስት በጨዋታው ሁለት ጊዜ መምራት ቢችልም ውጤቱን ማስጠበቅ አልቻለም።

ውጤቱን ተከትሎ ሊቨርፑል በተከታታይ ጨዋታዎች ነጥብ ጥሏል።

በመጀመሪያ ጨዋታው ሽንፈት ያስተናገደው ኖቲንግሃም ፎረስት በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ነጥቡን አግኝቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም