ቀጥታ፡

ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ከታይላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 22/2018 (ኢዜአ) ፦የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ከታይላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲሃሳክ ፉዋንግኬትክየው ጋር በብሔራዊ ቤተመንግሥት ተወያይተዋል። 

የታይላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲሃሳክ ፉዋንግኬትክየው ለይፋዊ የስራ ጉብኝት እና ታሪካዊውን “የታይላንድ-አፍሪካ ኢኒሼቲቭ” በይፋ ለማስጀመር ዛሬ አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል።


 

ዛሬ ከሰዓት ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጋር በብሔራዊ ቤተመንግሥት ተወያይተዋል።

በኢትዮጵያ እና በታይላንድ መካከል እያደገ የመጣውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ወደ ላቀ ደረጃ ማሻገር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውም ተገልጿል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም