ቀጥታ፡

ማንችስተር ሲቲ ከክሪስታል ፓላስ ጋር ጨዋታውን ያደርጋል

 

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 22/2018 (ኢዜአ)፦ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ይጀመራል።

ምሽት አራት ሰዓት ላይ ክሪስታል ፓላስ ከማንችስተር ሲቲ በሰልኸረስት ፓርክ ይጫወታሉ።

በመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብር ክሪስታል ፓላስ በኤቨርተን የ2 ለ 0 ተሸንፏል።

አዲሱ የፓላስ አሰልጣኝ ፒዬር ሴጅ የአሰልጣኝነት ቆይታቸውን በሽንፈት ጀምረዋል።

በአንጻሩ የማንችስተር ሲቲው አዲስ አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ በመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታ ቡድናቸው ቦርንማውዝን 2 ለ 1 አሸንፏል።

ሁለቱ ክለቦች በፕሪሚየር ሊጉ እርስ በእርስ ሲገናኙ የአሁኑ ለ33ኛ ጊዜ ነው። ከዚህ ቀደም ባደረጓቸው 32 ጨዋታዎች ማንችስተር ሲቲ 20 ጊዜ ሲያሸንፍ ክሪስታል ፓላስ አራት ጊዜ ድል ቀንቶታል። በቀሪ ስምንት ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል።

ማንችስተር ሲቲ በጨዋታዎቹ 75 ግቦችን ሲያስቆጥር ክሪስታል ፓላስ በበኩሉ 28 ጎሎችን ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ክሪስታል ፓላስ ለመጨረሻ ጊዜ ሲቲን በሊጉ ያሸነፈው እ.አ.አ በ2021 ነው።

ጨዋታው ማንችስተር ሲቲ ተከታታይ ድሉን ለማስመዝገብ ፣ ክሪስታል ፓላስ በአዲሱ የውድድር ዓመቱን የመጀመሪያ ሶስት ነጥቡን ለማግኘት የሚያደርጉት ነው።

የ42 ዓመቱ አንዲ ማድሊ ጨዋታውን በዋና ዳኝነት ይመሩታል።

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር እስከ ነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም