ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቻይናዋ ቼንዱ ከተማ አዲስ የካርጎ በረራ አስጀምሯል

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 22/ 2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቻይናዋ ቼንዱ ከተማ አዲስ የካርጎ በረራ በዛሬው ዕለት ማስጀመሩን አስታወቀ።

የተጀመረው የካርጎ በረራ በደቡብ ምዕራብ ቻይና እና አፍሪካ መካከል አዲስ የካርጎ ትራንስፖርት መስመር የከፈተ መሆኑን አስታውቋል፡፡

አገልግሎቱ በምዕራብ ቻይና እና በአፍሪካ መካከል ያለውን የንግድ እና የኢኮኖሚ ትስስር የሚያጠናክርና የሚደግፍ መሆኑን የኢትዮጵያ የአየር መንገዱ አመልክቷል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም