የታይላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
የታይላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ ፤ነሐሴ 22/2018 (ኢዜአ)፦ የታይላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲሃሳክ ፉዋንግኬትክየው ለይፋዊ የስራ ጉብኝት እና ታሪካዊውን “የታይላንድ-አፍሪካ ኢኒሼቲቭ” በይፋ ለማስጀመር አዲስ አበባ ገብተዋል።
ሚኒስትሩ ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ብርሃኑ ጸጋዬ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲሃሳክ ፉዋንግኬትክየው በአዲስ አበባ ቆይታቸው ከመንግስት ከፍተኛ አመራሮች ጋር በሁለቱ ሃገራት ግንኙነት ዙሪያ ውይይት አንደሚያደርጉም ተገልጿል።
ይህ ጉብኝት በኢትዮጵያ እና በታይላንድ መካከል እያደገ የመጣውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግርና የአፍሪካ-ታይላንድ ትብብርን የሚያጠናክር አዲስ ምዕራፍ ስለመሆኑም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።