ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ እና ደቡብ ኮሪያ ታሪካዊና ዘመናትን የተሻገረው ወዳጅነት ወደ ላቀ ምዕራፍ ተሸጋግሯል

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 20/2018 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ እና ደቡብ ኮሪያ መካከል ያለው ታሪካዊና ዘመናትን የተሻገረው ወዳጅነት ወደ ላቀ ምዕራፍ መሸጋገሩን ተሰናባቹ በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር ጃንግ ካንግ ገለፁ።

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር የነበሩትን አምባሳደር ጃንግ ካንግን አሰናብተዋል።


 

በብሔራዊ ቤተ መንግሥት በተከናወነው የስንብት መርሃ ግብር ተሰናባቹ አምባሳደር ጃንግ ካንግ እንዳሉት፤ የኢትዮጵያ እና ደቡብ ኮሪያ ወዳጅነት በጠንካራ ታሪካዊ መሠረት ላይ የተገነባ ነው።

የሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት በስትራቴጂክ ጉዳዮች ላይ እያደገ መምጣቱንም ጨምረው ገልጸዋል።

በተለይም በከፍተኛ ባለሥልጣናት ደረጃ በሚደረጉ ጉብኝቶች፣ በኢኮኖሚ ትብብርና በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ዘርፎች አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ በቆዩባቸው ዓመታትም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የበኩላቸውን ገንቢ ሚና መወጣታቸውን አምባሳደሩ ጠቁመዋል።

በቀጣይም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ ልውውጥ መጠን ማሳደግ የደቡብ ኮሪያ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ያላቸውን ኢንቨስትመንትና የኢኮኖሚ ተሳትፎ ማጠናከር እንደሚገባም ተናግረዋል።

በተጨማሪም በሕዝቦች መካከል ያለውን የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትና የባህል ልውውጥ የበለጠ ማጎልበት ይገባል ነው ያሉት።

የሁለቱ ሀገራት ታሪካዊና ጠንካራ ወዳጅነት በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን ተስፋ ገልጸው፤ በኢትዮጵያ በነበራቸው መልካም የስራ ጊዜ ለተደረገላቸው ትብብር ምስጋና አ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም